Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስናት ፈጋግ ድንበር ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽን ፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስናት የጋምቤላ ክልል ፈጋግ ድንበር የመጀመሪያው ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ ዛሬ በማስመረቅ ሥራ ጀመረ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክታር አቶ ሙጂብ ጀማል በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ወቅት እንዳሉት የመቆጣጠሪያ ኬላው የሁለቱ ሀገራትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል።

በተለይም በአካባቢው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርንና አሁን ላይ የሀገራት ስጋት የሆነውን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ጭምርጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ዘንድሮ ብቻ የጋምቤላ ክልልን ጨምሮ ሀገሪቱ በምትዋሰንባቸው አራት ቦታዎች ዘመናዊ የመቆጣጠሪየ ኬላ መክፈቱን የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ታመሩ ገንቦቶ ተናግረዋል።

ይህም በሀገሪቱ ያሉት መቆጣጠሪያ ኬላ ቁጥር ወደ 16 ከፍ እንዳደረገው ጠቁመው በቅርቡ ቤኒሻንጉልን ጨምሮ በሌሎች ጠረፋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጨማሪ ኬላዎችን ለመክፍት ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።

በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ የፍልሰት ቁጥጥር ኃላፊ ሚስተር ማሌንጎ ሞንጋ በበኩላቸው ሰፊ የሆነው የአፍሪካዊያን ፍልስት የሚካሄደው በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.