Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት በሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሸነፍ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ዕውን የሚያደረግ አመራር ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት በየጊዜው በሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሸነፍ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ዕውን የሚያደረግ አመራረ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ያሉት በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ሲሰጥ የነበረውን የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ማጠናቀቂያ መድረክ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ ችግሮች ቢበዙም የነገዋ ኢትዮጵያ ግን በብሩህ ተስፋ የተሞላች ናት ብለዋል።

በመሆኑም አመራሩ በየጊዜው በሚያጋጥሙ ችግሮች ሳይሸነፍ የተሻለ ነገን ዕውን ለማድረግ ሊተጋ ይገባል ነው ያሉት።

ኃላፊነት የተሰጣቸው አመራሮችም ስራዎቻቸውን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲከውኑ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ላለፉት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአዳዲስ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና በሁሉም ክልሎች ተሿሚ አመራሮች ዘንድ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.