Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የምግብና የመጠጥ ወጪ ንግድ ምርቶቿን በምዕራብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ ላይ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ አፍሪካ የምግብና መጠጥ አውደ ርዕይ በናይጄሪያዋ ዋና ከተማ ሌጎስ ትናንት ተከፍቷል፡፡

በአውደ ርዕዩ የኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሪነት ድርሻውን በመውሰድ እና በማስተባበር ኢትዮጵያ፣ “የኢትዮጵያን ሃገር በቀል እና የተፈጥሮ ምርቶች ይግዙ” በሚል መሪ ቃል ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል፡፡

የተለያዩ የሴክተር መስሪያ ቤቶችም ሴክተሮቻቸውን ወክለው መሳተፋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

አውደ ርዕዩ ኢትዮጵያ ዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶቿን ለዓለም አቀፉ የንግድ ማሕበረሰብ በማቅረብ በአፍሪካ ውስጥ የሚኖራትን የንግድ ግንኙነት የምታጠናክርበትንና በዓለም አቀፍ ደረጃ የምትታይበትን አጋጣሚ ለመፍጠር ያግዛታል ነው የተባለው።

አውደ ርዕዩ እስከ ነገ የሚቆይ ሲሆን፥ ኢትዮጵያም በተፈጠረው ምሕዳር ተጠቅማ የንግድ ግንኙነቶችን በመፍጠር፣ የንግድ ልውውጦች እና ውይይቶች እንዲሁም የገበያ ዕድሎችን የመለየት ሥራ እንደምትሰራ ተመልክቷል፡፡

በተጨማሪም መንግስት ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር ተወያይቶ የገበያ ዕድሎች የሚፈጠሩበትን ምህዳር ለማመቻቸት እንደሚረዳ ከኢትዮጵያ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.