Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለመገንባት በትክክለኛ ጎዳና ላይ ትገኛለች – አምባሳደር ሂሩት ዘመነ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤልጅየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለመገንባት በትክክለኛ መንገድ ላይ መሆኗን ገለጹ።
አምባሳደር ሂሩት በብራሰልስ በተካሄደው ስብሰባ በትግራይ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን አመላክተዋል።
ይህም ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን እና የሀገር አንድነትና ሉዓላዊነትን የመጠበቅ ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስም፥ አሁን ያለው ሁኔታም የፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑን አብራርተዋል።
ከህግ ማስከበር እርምጃው ጋር በተያያዘም 40 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች ወደ ሱዳን ገብተዋልም ነው ያሉት፡፡
በአካባቢው ያሉትን ንጹሃን ዜጎች ለመርዳት እና ለመጠበቅ መንግስት የሰብአዊ መተላለፊያ መንገድ መክፈቱን ጠቅሰው ይህ ተደራሽነት እየሰፋ እንደሚሄድም አስረድተዋል፡፡
ተልዕኮው ከተጠናቀቀ በኋላም ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከሱዳን ጋር ውይይት ስለመደረጉም አንስተዋል፡፡
አምባሳደሯ አያይዘውም በኢትዮጵያ ኮቪድ 19፣ ጎርፍ እና በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች በተከሰተው የአንበጣ መንጋ ሳቢያ ሰብዓዊ ችግር እንደነበር ጠቁመዋል ፡፡
መሰል አጋጣሚዎች ሁኔታውን የበለጠ ፈታኝ አድርጎታል ያሉት አምባሳደሯ÷ ዓለም አቀፍ አጋር አካላት ላደረጉት ድጋፍና የአውሮፓ ህብረት በቅርቡ ለስደተኞቹ ድጋፍ ለመስጠት ቃል መግባቱን አስታውሰው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።
አምባሳደሯ አያይዘውም የኢትዮጵያ ቀዳሚ ትኩረት በልማት እቅዶች እና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የህዝቡን ኑሮ ማሻሻል ነው ብለዋል፡፡
በማብራሪያቸውም የሃገሪቱን አዲሱን የ10 ዓመት የልማት ዕቅድን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ዕቅዱ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በፆታ እኩልነት እና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ ያተኩራልም ነው ያሉት ፡፡
ምንጭ፡-ዘ ብራሰልስ ታይምስ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.