Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ድንበር ከሚጋሯት ሀገራት በላይ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ሟቾችን አስመዝግባለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ድንበር ከሚጋሯት ሀገራት በላይ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው እና ሟቾችን አስመዝግባለች።
ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 91 ሺህ 693 ሰዎችን እና 1 ሺህ 396 ሟቾችን በማስመዝገብ ድንበር ከሚጋሯት ስድስት ሀገራት ቀዳሚዋ ናት።
ከኢትዮጵያ በመቀጠል ኬንያ 47 ሺህ 212 ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ 870 ሟቾችን ያስመዘበች ሀገር መሆኗ ተጠቁሟል።
ሌላኛው ከኢትዮጵያ ጋር ሰፊ ድንበር የምትጋራው ሱዳን 13 ሺህ 724 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ስታስመዘግብ 836 ሰዎች ደግሞ በበቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።
ጅቡቱ 5 ሺህ 522 በቫይረሱ የተያዙ እና 61 ህይወታቸው ያለፈ፣ ሶማሊያ 3 ሺህ 897 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ እና 102 ሟቾችን፣ ደቡብ ሱዳን 2 ሺህ 872 ቫይረሱ ያለባቸው እና 55 ህይወታቸው ያለፈ እንዲሁም ኤርትራ 457 ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ምንም ሞት ያልተመዘገበባት ሀገር ሆና ቀጣዩን ደረጃ ይዘዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.