Fana: At a Speed of Life!

በፕሪምየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እና በክልል ከተማዎች ተካሂደዋል፡፡

በዚህም ከተካሄዱት ሰባት ጨዋታዎች ስድስቱ በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ አንዱ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ሰበታ ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

በሌላ ጨዋታ ወደ ሀዋሳ ከተማ ያቀናው አዲሱ አዳጊ ወልቂጤ ከተማ በሀዋሳ ከተማ 3 ለ 1 ተሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ ወደ ጅማ ያቀናው ወላይታ ድቻ በአዲስ አሰልጣኝ እየተመራ ጀማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

የውጤት ቀውስ ውስጥ የነበረው ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማ 2 ለ 1 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስጥ ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡

ባህርዳር ከተማ ወልዋሎ አዲግራትን ያስተናገደበት ሌላው የሳምንቱ ጨዋታ በባህርዳር ከተማ 3 ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በዛሬው ዕለት ከተካሄዱት ጨዋታዎች ብቸኛ የአቻው ውጤት የተመዘገበበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሆሳዕና ከተማ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ነው የተጠናቀቀው፡፡

ውጤቱን ተከትሎ መቐለ 70 እንዳርታ በአራት ነጥብ ልዩነት በ19 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት የጀመረ ሲሆን ፋሲል ከነማ እና ስሑል ሽረ በጎል ልዩነት ተበላልጠው በእኩል 15 ነጥብ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.