Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ-ኬንያን የሚያገናኝ የመቆጣጠሪያ ኬላ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያገናኝ የነብረሙዝ መቆጣጠሪያ ኬላ ተመረቀ፡፡
ኬላውን መርቀው የከፈቱት የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል እንዳሉት÷ እንደነዚህ አይነት የየብስ ኬላዎች ድንበር አከባቢ የሚኖሩ ዜጎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለማሳለጥ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ለመቆጣጠርና የስራ ዕድል ለመፍጠር ፣የሀገሪቷን የኢሚግሬሽን የየብስ ኬላዎች ለማዘመን፣ለማስፋፋትና ለማጠናከር ትልቅ ሚና አለው፡፡
ኬላው የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከአይ ኦ ኤም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያስገነባው መሆኑ ተገልጿል።
በተመሳሳይ መልኩ በቀጣይ በጋምቤላ፣በቤንሻንጉልና በሶማሌ ክልሎች የሚመረቁና የሚገነቡ አዳዲስ ኬላዎች መኖራቸው ታውቋል።
ኤጀንሲው በባለፉት ዓመታት በርካታ የየብስ መቆጣጠሪያ ኬላዎችን መክፈቱ የተገለፀ ሲሆን ÷ከእነዚህ ውስጥ ባለፉት ወራት በአፋርና ሶማሌ ክልሎች ተመርቀው የተከፈቱት ሁለት የመቆጣጠሪያ ኬላዎች እንደሚጠቀሱ ከኢሚግሬሽን ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.