Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀከቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀከቶችን ጎብኝተዋል።

በዚህም የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር፣ የሸገር ቤተ መጽሀፍት፣ የታላቁ ቤተ መንግስት ፓርኪንግና የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክቶችን የስራ አፈፃፀም ተመልክተዋል።

ኢንጂነር ታከለ የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ እንደሆነ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው መርሀ ግብር እንዲጠናቀቁ የበለጠ ጥረት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

በቀጣይ ቀናትም የፕሮጀክቶቹ ግንባታ ሂደት በዝርዝር ይገመገማል መባሉን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.