Fana: At a Speed of Life!

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኙ የማዕድን ማውጫ ቦታዎችን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን ጎብኝተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኙ የማዕድን ማውጫ ቦታዎችን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን ተመልክተዋል።
 
ሚኒስትሩ አሻሽሬ አካባቢ ወርቅ በማውጣት ሂደት ላይ የሚገኘውን “አስኮም ማይኒንግ” ከተመለከቷቸው ቦታዎች አንዱ ነው ተብሏል።
 
ኩባንያው በአካባቢው ወርቅ እና የከበሩ ማዕድናትን በማፈላለግ ሂደት ላይ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ወደ ምርት ለመግባት የሚያስችለውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።
 
ሚንስትሩ በበኩላቸው ተቋሙ በፍጥነት ወደ ምርት መግባትና ሃገሪቷ ከዚህ ሃብት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
 
በሂደቱም የአካባቢው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ዋነኛ ትኩረት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
 
ሚኒስትሩ ከጉብኝቱ በተጨማሪም በክልሉ ከሚገኙ የማዕድን አልሚዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
 
አልሚዎቹ ከማዕድን ልማት ጋር በተያያዘ የመሰረተ ልማት ችግርና የፀጥታ ጉዳዮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዳይገቡ እንቅፋት እንደሆነባቸውም አንስተዋል።
 
በክልል ብዙ ሀብት መሆን ያለባቸው ፀጋዎች እንዳሉ የተናገሩት ኢሚኒስትሩ እነዚህ ሀብቶች በተገቢው መንገድ ስራ ላይ እንዲውሉና ችግሮች እንዲፈቱ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከክልሉ ጋር በመሆን እንደሚሰራ ገልፀዋል።
 
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘርፋ በዘመናዊ መልኩ እንዲያድግ እየሰራ ስለመሆኑ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.