Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድን ጠንካራና ተፎካካሪ ድርጅት ለማድረግ እንደሚሰሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ድርጅቱ ጠንካራ ሆኖ እንዲወጣ በትጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ኢጋድ ለ34 ዓመታት ገደማ ከፊል የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትን አባል አድርጎ ሁሉን ዓቀፍ ቀጠናዊ ተግባራትን ሲከውን መቆየቱን ጠቅሰው፥ ለዚህ ደግሞ የአስተዳደርና የአደረጃጀት ስራዎችን በአዲስ መልክ ማደራጀት ዋናው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢጋድ አደረጃጀቱንና የቆዩ ሕጎችን መከለስ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ መድረሱን አንስተው፥ አደረጃጀቱ ሲከለስ የአባል ሃገራቱ ስብጥርም ታሳቢ ይደረጋል ብለዋል።

የቆዩ ሕጎች እየተተገበሩ በመሆኑ የአባልነት መዋጮ መሰብሰብ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው ያሉት ዶክተር ወርቅነህ፥ የተለያዩ መተዳደሪያ ሕጎች ሳይሻሻሉ ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ተለይታ ራሷን የቻለች ሃገር መሆኗን ለአብነት ጠቅሰዋል።

ኢጋድ በአባል ሃገራቱ ውስጥ የሚገኙ የተሻሉ ተማሪዎችን እርስ በእርስ የትምህርት ዕድል እየሰጠ ቀጠናዊ ትስስሩን ለማጠናከር ማሰቡንም ጠቁመዋል።

ዋና ጸሐፊው አያይዘውም ኢትዮጵያ በቀጠናው ትልቅ ሃገር እንደ መሆኗ በተቋሙ ውስጥ ያላትን የጎላ ሚና አጠናክራ እንትቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.