Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ ለአካባቢያዊ ውህደት እንደሚሰራ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስት ኢጋድ ለአህጉራዊ ውህደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡
የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተቋሙ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ አጐራባች ህዝቦች መሀከል በጤና፣ በግብርናና በሌሎች መስኮች መደጋገፍ እንዲኖር በማድረግ ክፍለ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደት እንዲኖር ይሰራል ብለዋል፡፡
ዶክተር ወርቅነህ የኢትዮጵያ አዋሳኝ በሆነው የመንዴራ ክልል የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን የሁለቱንም አገሮች ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ድጋፎችን ለመንዴራ ክልል አስተዳዳሪ አሊ ሮባ አስረክበዋል፡፡
በመንዴራ ቆይታ ያደረጉት በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም በድንበሮቻችን አካባቢ የሚገኙ ህዝቦችን የልማት ተጠቃሚ በማድረግ ለሰላም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ኢጋድ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ቡድኑ በመንዴራ የሚገኙ የልማት ስራዎችን መጎብኘቱን ኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.