Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ የካንሰር ልህቀት ማዕከል የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ የካንሰር ልህቀት ማዕከል የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡

የመክፈቻ ስነ-ሥርዓቱ የኢጋድ ሥራ አስፈፃሚ፣ የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት እና የተቋሙ የልማት አጋሮች ተገኝተዋል፡፡

የልህቀት ማዕከሉ በ500 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ነው ግንባታው የሚካሄደው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማዕከሉ ግንባታ የ200 ሺህ ሜትር ስኩዌር መሬት አበርክቷል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2012 በኢጋድ ምክር ቤት ውሳኔ የተቋቋመው ይህ ማዕከል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካንሰርን ለመዋጋት ቁልፍ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማዕከሉ ሲጠናቀቅም የካንሰር ምርመራን፣ ህክምናን እና የተለያዩ ምርምሮችን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራት ያላቸው የካንሰር እንክብካቤ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ከኢጋድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ማዕከሉ በቀጠናው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የካንሰር-ነክ የጤና እንክብካቤ ችግርን ለመቋቋም እና የካንሰር በሽታን የመከላከል እና የማከም ችሎታ ያላቸው ብቁ ባለሙያዎችን ማሰልጠንን ያለመ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.