Fana: At a Speed of Life!

ኤምባሲው ተቀማጭነታቸውን ካይሮ አድርገው ኢትዮጵያን ለሚሸፍኑ አምባሳደሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ተቀማጭነታቸውን ካይሮ አድርገው ኢትዮጵያን ለሚሸፍኑ አምባሳደሮች በትግራይ ክልል በተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ዙሪያ ገለፃ አደረጉ።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ገለፃ ላይም የቦስኒያና ሄርዞጎቪኒያ፣ የክሮሺያ፣ የኢኳዶር፣ የኢስቶኒያ፣ የላቲቪያ፣ የማልታ፣ የማይናማር፣ የኔፓል፣ የፓናማ እና የፊሊፒንስ ኤምባሲዎች አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል።

አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ለአምባሳደሮቹ ባደረጉት ገለፃም፥ መንግስት ትክክለኛ እና አካታች ስርአት ለመዘርጋት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አያይዝወም የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር ባካሄደው ዘመቻ እና ከዘመቻው በኋላ እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መንግስት የህግ የማስከበር ዘመቻው በተካሄደባቸው አካባቢዎች ዜጎች እንዳይጎዱ አስፈላጊውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እየሰራ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በንግግር ለመፍታት ያላትን ዝግጁነት ገልጸው በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተጀመረው የሶስትዮች ድርድር ዳግም እንደሚጀመር እምነቴ ነው ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በስኬት መጠናቀቁን ያስታወቁት አምባሳደር ማርቆስ፥ ይህም በሀገሪቱ ትክክለኛ የዴሞክራሲ ስርዓትን ለመገንባት መሰረት የሚጥል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው በግብፅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ግልፅ እና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ስላስቻላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.