Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው በመዲናዋ ለ1 ሺህ 893 መንገዶች ስያሜና ለ862 ሺህ 69 ቤቶች የቤት ቁጥር ለመስጠት እየሰራ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ዘመናዊ የአድራሻ ስርዓት አገልግሎት እንደሚዘረጋ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በ 100 ወረዳዎች ላይ ዘመናዊ የአድራሻ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለ1 ሺህ 893 መንገዶች ስያሜ እንደሚሰጥ የኤጀንሲው ኮሙየኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ገልጿል።

ከመንገዶቹ ጋር ለተያያዙ 862 ሺህ 69 ቤቶች የቤት ቁጥር እንደሚሰጥም ነው ያስታወቀው።

በተያዘው በጀት ዓመት ለ292 መንገዶች የአድራሻ ካርታ እንደሚያዘጋጅ የገለፀው ኤጀንሲው ለ53 ዋና ዋና መንገዶችና ከመንገዶቹ ጋር ለተያያዙ 67 ሺህ 500 ቤቶች ገደማ የቤት ቁጥር በመስጠት ለአድራሻ አገልግሎት ክፍት እንደሚያደርግ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ዘሪሁን አምደማሪያም ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው የአድራሻ ስርዓት መረጃን ለሚፈልጉ ተቋማትና ግለሰቦች መረጃን በቀላሉ የሚያገኙበትን መንገድ ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

 

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

 

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

 

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

 

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.