Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው የኮቪድ19 ክትባት ማሰራጨቱን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የኮቪድ19 ክትባትን ለሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ማሰራጨቱን የኤጀንሲው የስርጭት ቡድን መሪ አቶ ተስፋሁን አብሬ አስታወቁ።

የክትባት ስርጭቱ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው የስርጭት ቁጥር መሠረት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ለኦሮሚያ ፣ለአማራ ፣ ለደቡብ ብሔር ብሔረሠቦችና ሕዝቦች ፣ ለሲዳማ ፣ ለጋምቤላ፣ ለትግራይ፣ ለአፋር፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ለሶማሌ፣ ለሀረሪና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንደተሰራጨ ተገልጿል፡፡

በስርጭቱ ወቅት ቅዝቃዜው በትክክል መጠበቁን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ በሁሉም ተሽከርካሪዎች ላይ መገጠሙንና ይህም ክትባቱ ጥራቱ እንደተጠበቀ ለጤና ተቋማት መድረሱን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል።

ኤጀንሲው 2 ሚሊየን 184 ሺህ ዶዝ የክትባት መድኃኒት የተረከበ ሲሆን ለክትባት አገልግሎቱ የሚውል አልኮል እና ሲሪንጅ ማሰራጨቱ ተጠቁሟል።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.