Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ጤና ተቋማት መድሐኒት በቀጥታ የሚያገኙበትን ፕሮግራም በወላይታ ዞን በይፋ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ጤና ተቋማት መድሐኒት በቀጥታ የሚያገኙበትን ፕሮግራም በወላይታ ዞን በይፋ ጀምሯል::

ከዚህ ቀደም ወረዳዎች ለጤና ተቋማት መድኃኒቶችን ለማድረስ የሚያወጡትን ወጪ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል ተብሏል፡፡

በሃገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነው ‘ላስት ማይል ደሊቨሪይ ፓይለት ፕሮጀክት’ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሚገኙ ጤና ተቋማት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሲዳማ በሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ለሚገኙ 109 ጤና ተቋማት መድኃኒቶችን በየወሩ በቀጥታ ከተቋማችን እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ይህንን መነሻ በማድረግ በወላይታ ዞን አስተዳደር ዉስጥ የሚገኙ 50 ጤና ተቋማትን የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚያርግ የመግባቢያ ሠነድ ከወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤቶችና ከጤና ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በመፈራረም ነው በይፋ የተጀመረው፡፡

እስካሁን 36 ጤና ተቋማት መድኃኒቶችን በየወሩ በቀጥታ ከተቋማችን ማግኘት መጀመራቸውም ተነግሯል፡፡

በቀጣይም ቀሪዎቹ ጤና ተቋማት መድኃኒቶችን በየወሩ በቀጥታ ከኤጀንሲው መጋዘኖች እንዲያኙ በማድረግ በጤና ተቋማት የመድኃኒት አቅርቦቱንና የክትባት ደህንነትን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ከኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.