Fana: At a Speed of Life!

እህል የጫኑ ተጨማሪ ሁለት መርከቦች ከዩክሬን ተነስተዋል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ተጨማሪ ሁለት የወጪንግድ እህል የጫኑ መርከቦች ከዩክሬን ጥቁር ባሕር ወደቦች መነሳታቸውን የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው በተደረሰው ሥምምነት መሠረት የመጀመሪያዋ የወጪ ንግድ እህል የጫነች መርከብ ባለፈው ሳምንት ከዩክሬን ጭና ከወጣች በኋላ አጠቃላይ የወጪ ንግድ እህል የጫኑ መርከቦች ቁጥር 10 ደርሷል፡፡

በዛሬው ዕለትም ሳኩራ የተሰኘችው መርከብ ከዩዝኒ 11 ሺህ ቶን አኩሪ አተር ጭና እንደተነሳችና ወደ ጣሊያን እንደምታመራ ተገልጿል፡፡

አሪዞና የተሰኘችው መርከብ ደግሞ ከቼርኖሞርስክ 48 ሺህ 458 ቶን የወጪ ንግድ በቆሎ ጭና በደቡባዊ ቱርክ ወደምትገኘው ኢስኬንደሩን ትጓዛለች ተብሏል፡፡

ትናንት ከዩክሬን ወደቦች የተነሱት ሙስጠፋ ኒካቲ፣ ስታር ሄለና፣ ግሎሪ እና ሪቫ ዊንድ የተሰኙ አራት የወጪ ንግድ እህል የጫኑ መርከቦች በአጠቃላይ 170 ሺህ ቶን የሚጠጋ የግብርና ምርቶች መጫናቸውን የሀገሪቷ የመሠረተ ልማት ሚኒስትር አሌክሳንደር ኩብራኮቭ መናገራቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

አራቱ መርከቦች ዛሬ ማምሻውን ኢስታንቡል ይደርሳሉ ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.