Fana: At a Speed of Life!

እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመመስረት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ነሀሴ 7 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመመስረት መስማማታቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱ አገራት ለማስማማት ሲያሸማግሉ መቆየታቸው ተነግሯል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፣ የአብዲቢው ልዑል መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋራ በሰጡት መግለጫ ÷ ስምምነቱ በመካከለኛው ምስራቅ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን መሰረት እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።

ከዚያም ባለፈ ስምምነቱ እስራኤል የፍልስጤም ግዛት በሆኑ የዌስት ባንክ አካባቢዎችን ወደ ራሷ ለመጠቅለል ያላትን እቅድ ያስቀራልም ነው ያሉት ።

በአሜሪካ የዩናይትድ አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር ዮሱፍ አል ኦታይባ በበኩላቸው÷ስምምነቱ ለዲፕሎማሲ እና ለአካባቢው ሰላም ትልቅ ድል ነው ብለዋል ።

አክለውም በአረብ-እስራኤል ግንኙነት መካከል ያለውን ውጥረት የሚቀንስና ለአዎንታዊ ለውጥ አዲስ ኃይል የሚፈጥር ትልቅ እድገት ነው ሲሉ አወድሰውታዋል ።

እስራኤል እስካሁን ድረስ ከዓረብ ባሕረ ሰላጤ አገሮች ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳልነበራት ይታወቃል።

ሆኖም ባላቸው የኢራን አካባቢያዊ ተጽዕኖ የጋራ ስጋቶች በመካከላቸው መደበኛ ያልሆነ ግንኙነት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱ እስራኤል ነፃነቷን በ1948 ካወጀች በኋላ ሦስተኛው የእስራኤል-አረብ የሰላም ስምምነት መሆኑ ተጠቅሷል ፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና አልጀዚራ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.