Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ህክምናን ለማገዝ የህክምና ቡድን ልትልክ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ህክምና ድጋፍ የሚያደርግ የህክምና ቡድን ልትልክ ነው።

የህክምና ባለሙያዎችን ያካተተው ልዑኩ ከሳምሶን አሱታ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ ሲሆን በዶክተር አሳፍ ፔሬዝ የሚመራ ነው።

ልዑኩ በኢትዮጵያ ለሁለት ሳምንታት የኮሮና ቫይረስ ህክምና በመስጠት ድጋፍ እንደሚያደርግ ዋይ ኔት ኒውስ ዘግቧል።

የልዑኩ መሪ ዶክተር አሳፍ ፔሬዝ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እስራኤል ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ጋር ተያይዞ ድጋፍ የሚያርግ ቡድን ወደ ሌሎች ሀገራት መላኳ ከህልም ያልዘለለ ነበር ብለዋል።

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ እስራኤል ያላትን ልምድ እና እውቀት የማጋራት ግዴታ አለባት ሲሉም ነው የገለፁት።

ለእስራኤል እንደዚህ አይነት ተልዕኮ ትልቅ ኩራት እና የክብር ምንጭ መሆኑን የቡድን መሪው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ ሲሆን ከባይረሱ ጋር ተያይዞ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥርም ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.