Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በጋዛ እና ሶሪያ በሚንቀሳቀሰው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ይዞታ ላይ ጥቃት ፈጸመች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እና በሶሪያ በሚንቀሳቀሰው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።

የሃገሪቱ ጦር በደቡባዊ ደማስቆ እና ጋዛ በመሸገውና ራሱን የፍልስጤም እስላማዊ ታጣቂ ብሎ በሚጠራው ቡድን ይዞታዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።

የአሁኑ ጥቃት እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ ለተወነጨፈባት የሮኬት ጥቃት አፀፋዊ ምላሽ መሆኑንም ነው ጦሩ የገለጸው።

የፍልስጤም እስላማዊ ታጣቂ ቡድን፥ ወደ ደቡባዊ እስራኤል ለተወነጨፉት 20 ሮኬቶች ሃላፊነት መውሰዱን ቀደም ብሎ ገልጾ ነበር።

እስራኤል ከተፈጸመባት የሮኬት ጥቃት ቀደም ብላ በጋዛ ድንበር አቅራቢያ ተቀጣጣይ ፈንጅ ለመቅበር ሞክሯል ያለችውን ፍልስጤማዊ መግደሏን ገልጻለች።

ቡድኑም ለፍልስጤማዊው ግድያ አፀፋ ነው በሚል በእስራኤል ላይ የሮኬት ጥቃት ሲፈጽም እስራኤልም የአፀፋ እርምጃ ወስዳለች።

በተፈጸሙት ጥቃቶች ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ ግን የተገለጸ ነገር የለም።

ሶሪያ በበኩሏ ከእስራኤል የተወነጨፉትን በርካታ ሚሳኤሎች ማክሸፏን አስታውቃለች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጨረሻ ያሉትን የመካከለኛው ምስራቅን የሰላም እቅድ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም በእስራኤል እና በፍልስጤማውያን መካከል አለመግባባቶች እየተካረሩ መጥተዋል።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.