Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በጋዛ የተመረጡ ቦታዎች የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟን ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በጋዛ በተመረጡ የሃማስ ይዞታዎች የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተሰምቷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ከጋዛ ወደ እስራኤል የተላኩ እና ተቀጣጠይ ነገሮችን የያዙ ፊኛዎች በደቡባዊ እስራኤል የእሳት አደጋ እንዲነሳ አድርገዋል፡፡

ይህን ተከትሎም እስራኤል በጋዛ የተመረጡ የሃማስ ይዞታዎች ላይ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህም በቅርቡ እስራኤል እና ሃማስ ለ 11ቀናት ያካሄዱት መጠነ ሰፊ ጦርነት በተኩስ አቁም ስምምነት ከተጠቋጨ በኋላ የተፈጸመ የመጀመሪያው ጥቃት ነው ተብሏል፡፡

በጥቃቱ በጋዛ እና ካህን ዩኒስ ከተማ ደቡባዊ ክፍል የሚገኙ የሀማስ ወታደራዊ ሰፈሮች ላይ ጉዳት ማድረስ መቻሉን ሚኒስቴሩ አንስቷል፡፡

በቀጣይ ከሃማስ የሽብር ቡድን ሊቀጣ የሚችልን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እስራኤል ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኗንም አስገንዝቧል፡፡

ሀማስ በበኩሉ በፍልስጤማውያን ዘንድ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና በእስራኤል ቁጥጥር ስር የሚገኙ ይዞታዎችን ለማስመለስ የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስጠነቀቀው፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ እስካሁን ከሁለቱም ወገኖች የደረሱ ጉዳቶች ዝርዝር ሁኔታ በዘገባው አልተገለጸም፡፡

ምንጭ ÷ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.