Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል እስከ ፈረንጆቹ 2050 የካርበን ልቀት መጠኗን 85 በመቶ ለመቀነስ ማቀዷን አስታውቃለች

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል እስከ ፈረንጆቹ 2050 የካርበን ልቀት መጠኗን 85 በመቶ ለመቀነስ ማቀዷን አስታውቃለች፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ÷ በፈረንጆቹ 2015 በፈረንሳይ የተፈረመውን የአየር ንብረት ለውጥ ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግ ሀገራቸው ሰፊ ስራዎችን እየሰራች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይህም በቀጣይ ሀገሪቷ ዝቅተኛ የካርበን ልቀት መጠን የተረጋገጠበት ኢኮኖሚ እንድትመራ የሚያስችላት እንደሆነ ነው ያመላከቱት፡፡

በዚህ መሰረትም ዕቅዱን ለማሳካት ከትራንስፖርት ዘርፉ፣ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲሁም ከከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ ለመቀነስ እና በታዳሽ ኃይል ለመተካት እየተሰራ ነው፡፡

እቅዱ ንፁህ ፣ ውጤታማ እና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለማረጋገጥ ከማስቻሉ ባለፈ ሀገሪቷን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ውጤታማ ስራ በመስራት ቀዳሚ ያደርጋታልም ነው ያሉት፡፡

በፈረንሳዩ የአየር ንብረት ለውጥ ማሻሻያ ስምምነት እስራኤልን ጨምሮ 200 ሀገራት ለተፈፃሚነቱ ፊርማ ማኖራቸው ይታወቃል፡፡

በወቅቱ እስራኤል እስከ 2030 የካርበን ልቀት መጠኗን 27 በመቶ ለመቀነስ ስትስማማ÷ በአንጻሩ አሜሪካ ከስምምነቱ ማፈንገጧ ይታወሳል፡፡

የኢንዱስትሪ አብዮትን ተከትሎ ዓለም በ1 ነጥብ2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እየሞቀች እንደምትገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ስለሆነም የዓለም መንግስታት በካርበን ልቀት ላይ አንዳች መፍትሄ በአፋጣኝ ማመላከት ካልቻሉ የሙቀት መጠን በአሳሳቢ ሁኔታ መጨመሩን እንደሚቀጥል በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ምንጭ÷ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.