Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል እና ባህሬን ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሊመሰርቱ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል እና ባህሬን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ዛሬ በይፋ ይመሰርታሉ፡፡

ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ ማናማ በሚደረግ ፕሮግራም የሚመሰረት መሆኑም ተነግሯል።

የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ባህሬን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶችን ተከትላ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ መስማማቷን ተከትሎ የመጣ ነው።

ይህን ተከትሎም እስራኤል ዛሬ ወደ ባህሬን የዲፕሎማቲክ ልዑኳን እንደምትልክ አስታውቃለች፡፡

የእስራኤል ልዑካን ቡድን በእስራኤል ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሜየር ቤን-ሻባት የሚመራ መሆኑም ታውቋል፡፡

በይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ምስረታው ላይ የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቲቭ ምኑቺን ይገኛሉም ነው የተባለው።

እንደ እስራኤል ባለስልጣናት ገለጻ የጋራ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ በእስራኤል እና በባህሬን መካከል ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይመሰረታል፡፡

ሃገራቱ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አደራዳሪነት ግንኙነታቸውን ለማደስ መስማማታቸው ይታወሳል።

በፈረንጆቹ 1979 ግብፅ እንዲሁም 1994 ዮርዳኖስ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች እና ባህሬን ቀደም ብለው ከእስራኤል ጋር ግንኙነታቸውን ያደሱ ሃገራት ናቸው።

ምንጭ፡-ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.