Fana: At a Speed of Life!

እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ተሰብስቧል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ ሊፈጠር የሚችል ተገቢነት የሌለው የዋጋ ግሽበትን ለመከላከልና የምርት እጥረት እንዳይከሰት በተሰራ የተቀናጀ ስራ ከክልል አምራች ኅብረት ሥራ ማኅበራት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ከተሰበሰበው ምርት ውስጥ ከ875 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻሉም ነው የተገለፀው፡፡

እንዲሁም የግብርና ምርቶች እንዲሰበሰቡና የምርት አቅርቦቱ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ለማድረግ የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ከክልል የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ አመራሮችና ከኅብረት ሥራ ማህበራት አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ከፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.