Fana: At a Speed of Life!

እስከ ፈረንጆቹ 2020 መጨረሻ ድረስ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በቁጥጥር ስር ሊውል ይችላል- ፋኦ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) እስከ ፈረንጆቹ 2020 መጨረሻ ድረስ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በቁጥጥር ስር ሊውል እንደሚችል አስታወቀ።
ድርጅቱ በኢትዮጵያ ምስራቅ አማራ ፣ ደቡብ ምስራቅ ትግራይ እና በምስራቅ ኦሮሚያ ከአንበጣ መንጋ ጋር ተያይዞ የከፋ ችግር መከሰቱን በመግለፅ ሰፊ የሰብል ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል።
እንዲሁም የንፋስ አቅጣጫው ወደ ደቡብ መዞሩ በሶማሌ ክልል እንዲሁም በኬንያ እና ኡጋንዳ የአንበጣ መንጋ ስጋት እንዲፊጠር ማድረጉ ተጠቁሟል።
አሁን ላይ ግን በቂ የአንበጣ መንጋ ማጥፊያ ኬሚካል ክምችት በመኖሩ ፣ ኬሚካል መርጫ አውሮፕላኖች እየተገኘ መሆኑ እና የገንዘብ ድጋፍ በመገኘቱ እስከ
ፈረንጆቹ 2020 መጨረሻ ድረስ የአንበጣ መንጋው በቁጥጥር ስር ሊውል ይችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው በኢትዮጵያ የፋኦ ቢሮ የፕሮግራም ባለሙያ የሆኑት ጃኮብ ዳሜሊኦ ለአሜሪካ የእንግሊዘኛው ድምፅ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከፋኦ ሊያገኛቸው የሚችላቸውን የአንበጣ መንጋ መቆጣጠሪያ ሀብቶች እንያሳደገ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
እስከ ፈንጆቹ ህዳር ወር አጋማሽም ከዘጠኝ እስከ አስር የሚደርሱ ኬሚካል መርጫ ሄሊኮፕተሮች ሊገኙ እንደሚችሉ ጃኮብ ዳሜሊኦ ገልፀዋል።
እስካሁን በተካሄደ የአንበጣ መቆጣጠር ስራ 1 ሚሊየን ቶን የሚገመት ሰብል ማዳን መቻሉን እና ከኬሚካል ርጭቱ ጋር በተያያዘ ግማሽ ሚሊየን አርሶ
አደሮች አሁንም የቁም እንስሳቶቻቸውን መመገብ ይችላሉ ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.