Fana: At a Speed of Life!

እነ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቤ ህግ ምስክር እንዲያሰማ ቀጠሮ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም፣ አስካለ ደምለው እና ከዚህ በፊት በዋስ በወጣው 5ኛ ተከሳሽ ጌትነት በቀለ ላይ ዐቃቤ ህግ ምስክር እንዲያሰማ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የዐቃቤ ህግ ምስክር እንዲሰማ የታዘዘው ተከሳሾቹ በችሎቱ ወንጀሉን አልፈጸምንም በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ነው።

ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ወንጀሉን ስለመፈጸማቸው የሚያስረዱ የሰው ምስክር ላሰማ ሲል ጠይቋል።

ችሎቱም ዐቃቤ ህግ አለኝ ያለውን ምስክር እንዲያሰማ ጥያቄውን ተቀብሏል።

በዚህ መሰረት ከመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ 10 ቀናት ያህል ምስክር እንዲያሰማ ፈቅዷል።

ተከሳሾቹ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ በነበረው ሁከት እና ብጥብጥ ብሔር እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ለጠፋው የሰው ህይወት እና ንብረት መውደም ጋር ተያይዞ መከሰሳቸው የሚታወስ ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ ተከሳሾቹ በችሎቱ ህግን መሰረት ያላደረገ ቃል ተናግረዋል በሚል ፍርድ ቤቱ በማስጠንቀቂያ አልፏቸዋል።

በሌላ በኩል ህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሚት የሸገር አውቶቡስ ማቆሚያ ላይ የፈነዳ ቦምብን ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 11 የድርጅቱ ሰራተኞች በ1 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በእነሀይላይ ተክሉ በሚል መዝገብ የተካተቱት 11 የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ከጥበቃ ጀምሮ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ናቸው።

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.