Fana: At a Speed of Life!

እኛ በተመቻቸ ሁኔታ እየኖርን ወገኖቻችን ተፈናቅለው ማየት አንፈልግም- በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩናይትድ ኪንግደም ኮቨንተሪ ፣ ሰቶክ ኦን ትሬንት እና ማንቸስተር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል ንጹሃን ዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ጥቃት በማውገዝ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ገንዘብ አሰባሰቡ፡፡
በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንደገለጹት÷ ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን የኢትዮጵያን አንድነት ለመናድ እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባር በአንድነት በመነሳት ማክሸፍ ይገባል፡፡
ባለፉት ሶስት አመታት የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ በተስፋና በፈታኝ ሁኔታዎች ታጅቦ በስኬት የቀጠለ መሆኑን አስታውሰው÷ መጠነ ሰፊ የሪፎርም አጀንዳዎች የተዘረጉ በመሆናቸውም ዳያስፖራው ባለው እውቀት እና ቴክኖሎጂ ሊጫወት የሚችለው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
የህወሓት ቡድን በንጹሃን ዜጎች ላይ የከፈተውን ጥቃት ቀጥሎ ህይወት እየቀጠፈና ዜጎችን እያፈናቀለ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
‹‹በውጪ ሀገራት በተመቻቸ ሁኔታ እየኖርን የሀገራችን ዜጎች ተፈናቅለው ማየት አንፈልግም›› ብላችሁ በወሰዳችሁት ተነሳሽነት ለተፈናቀሉ ዜጎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋችሁ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል አምባሳደሩ፡፡
የየከተሞቹ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሊቀመንበሮች በበኩላቸው ÷ ያጋጠመንን ፈታኝ ችግር ለመወጣት ሀላፊነቱን ለመንግስት ብቻ በመተው ሀገርን መታደግ በአንድ እጅ ማጨብጨብ በመሆኑ÷ መላው ህዝብ በአንድነት በመነሳትና ከመንግስት ጎን በመቆም ኢትዮጵያን ከጥፋት ሀይሎች መታደግ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በየከተሞቹ ነዋሪ የሆነው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተው÷ ማህበሩን ለማጠናከር ቀጣይ ተከታታይ ስራዎችን ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር እንደሚያከናውኑ ገልጸዋል፡፡
በበርሚንግሃም፣ በማንቸስተር፣ ኮቨንተሪ እና ሰቶክ ኦን ትሬንት የተካሄደው ድጋፍ በተለያዩ የዩናይትድ ኪንግደም ከተሞች እንደሚቀጥል በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.