Fana: At a Speed of Life!

እየተከለሰ ባለው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተከለሰ ባለው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ላይ ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ ፖሊሲውን ለተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ጠቅላላ ፈጻሚዎች ማውረድ ያለመ መሆኑም ታውቋል፡፡
እንዲሁም መድረኩ ፖሊሲውን በማርቀቅ ሂደት የነበረውን ተሳትፎ ወደ ሁሉም ተቋማትና ፈጻሚዎች በማስፋት ግብዓት ማሰባሰብና ወጥነት ያለው ግንዛቤ ማግኘት በማስፈለጉ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ያኒያ ሰይድ እንዳሉት ፖሊሲው ሃገራዊ ይዘት ያለው ቢሆንም ባለቤትነቱ የሚኒስቴሩና የተጠሪ ተቋማት በመሆኑ ተቋማቱ በጋራ የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡ ይጠበቃል።
ከመድረኩ የሚገኘውን ግብዓት በማካተትም በቀጣይ ሃገራዊና ዓለም አቀፋዊ መልክ በማስያዝ ለዘርፉ የሰው ሐብትና መረጃ ልማት፣ ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ መር የኢኮኖሚ ስርአት መገንባት የሚያስችል አቅም እና ፖሊሲውን ለመተግበር ወጥነት ያለው ግንዛቤ ደረጃ ላይ መድረስ ይገባል ማለታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.