Fana: At a Speed of Life!

እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማምጣት አመላካች ናቸው- የዳያስፖራ አባላት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ትክክለኛ እድገትና ብልፅግና ለማምጣት የሚያመላክቱ መሆኑን በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ገለጹ።
የኢትዮጵየ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አባላት በአዲስ አበባ የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
የዳያስፖራ አባላቱ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን፣ የታላቁ ቤተ መንግስት መኪና ማቆሚያን፣ አብርሆት ላይበራሪን፣ የአድዋ ሙዚየም፣ እደሳት የተደረገለትን የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እና እንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ ከተሳተፉት መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ዳያስፖራዎች የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ትክክለኛ እድገትና ብልፅግና እውን ለማድረግ የሚያመላክቱ መሆኑን ገልጸዋል።
ከኖርዌይ የመጡት ወይዘሮ ኢትዮጵያ ዓለማየሁ፤ የፕሮክቶቹ ግንባታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ያካተቱና የአገሪቷን ቀጣይ እድገትና ለውጥ አመላካች ናቸው ብለዋል።
“በአዲስ አበባ የጎነኘኋቸውን ፕሮጀክቶች በእጂጉ አድቄያለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
በለንደን የሚኖሩት ፋሪስ ሙሀመድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በጫና ወስጥም ሆና እየገነባቻቸው ያሉ ፕሮጀክቶች የቀጣዩን ብሩህ ተስፋ የሚያመላክቱ ናቸው ብለዋል።
የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በተቀመጠላቸው ጊዜ፣ እቅድና ደረጃ በመሆኑም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
በአሜሪካ የሚኖሩት አቶ አለማየሁ አበበ፤ በኢትዮጵያ በተለይም በቅርብ አመታት የተከናወኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ሁላችንንም አስደሰቶናል ብለዋል።
የዳያስፖራ አባላቱ በጎበኙት ሁሉ መደሰታቸውን ገልጸው ወደ ሚኖሩበት አካባቢ ሲመለሱ ስለ አገራቸው ለሌሎች ለማስረዳት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋገጥዋል።
በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን መጎብኘትና የልማቱ ደጋፊ መሆን እንዳለባቸውም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ አባልና የልዑኩ አስተባባሪ አቶ አለባቸው ደሳለኝ ዳያስፖራው ለአገሩ እድገት እያደረገ ያለው ሚና የሚበረታታ መሆኑን ተናገራዋል።
በቀጣይም ለኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና የድርሻቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አባላት ከጳጉሜ 3 ቀን 2013 ጀምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት በማድርግ ላይ ሲሆኑ ቀደም ሲል ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጎብኝተዋል።
ከዚህም በተጓዳኝ ደም በመለገስ፣ ችግኞችን በመንከባከብ እና ሌሎች ሰብአዊ ተግባራትንም እያከናወኑ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.