Fana: At a Speed of Life!

እድሳት ሲደረግለት የቆየው የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እድሳት ሲደረግለት የቆየው የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ተመረቀ።

ህንጻውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መርቀው ከፍተውታል፡፡

ታሪካዊውና የከተማዋ ምልክት የሆነው ህንፃ ጥር 17 ቀን 1957 ዓ.ም ማለትም ከ57 ዓመት በፊት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኋላ ለእድሳት በቅቷል፡፡

የከተማው አስተዳደር ህንፃውን እጅግ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የታደሰ ሲሆን፥ ለተገልጋይ ምቹና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ሁሉ ባሟላ መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን ታስቦም ነው የታደሰው፡፡

በእድሳቱ የህፃናት መዋያ፣ ቤተ-መጽሀፍት ፣ የስልጠናና የምርምር ክፍሎች፣ ክሊኒክ፣ የቴአትር አዳራሽ፣ ስብሰባ አዳራሾች፣ የሰራተኞች እና የባለጉዳዮች መመገቢያ አዳራሽ እና የተለያዩ ቢሮዎችን ያቀፈ ሲሆን፥ በቂ የመኪና ማቆሚያ ፣ አረንጓዴ ስፍራዎችንና የከተማ ግብርናን ጨምሮ የያዘ እንዲሆን ተደርጓል እድሳት ተደርጎለታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.