Fana: At a Speed of Life!

ኦብነግ ለአቶ ሙስጠፌ የእንኳን ደስአለዎት መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ለአቶ ሙስጠፌ መሐመድ የሶማሌ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስአለዎት መልዕክት አስተላለፈ፡፡
ፓርቲው ባስተላለፈው መልዕክት ከክልመንግሥት ጋር አብሮ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት አመላክቷል፡፡
ለክልሉ ዘላቂ ሠላምና ልማት የአቶ ሙስጠፌ ወደፊት መምጣት ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብሏል፡፡
በአጠቃላይ ኦብነግ ከሶማሌ ክልል አዲሱ መንግስት ጋር አብሮ መሥራቱን ይቀጥላል ያለው መግለጫው÷ በጋራ መተማመን ላይ የተመሰረተ ገንቢ ሥራዎችን እንደምንሠራ እምነታችን ነው ብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.