Fana: At a Speed of Life!

ከህወሓት እና ከኦነግ ሸኔ ጋር በመቀናጀት ተልዕኮ በመፈጸም ላይ እያሉ ተይዘዋል የተባሉ ስድስት ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከህወሓት እና ከኦነግ ሸኔ ጸረ ሰላም ቡድኖች ጋር በመቀናጀት ተልዕኮ በመፈጸም ላይ እያሉ ተይዘዋል የተባሉ ስድስት ግለሰቦች ፍርድቤት ቀረቡ።
እነዚህ ተልዕኮ በመፈጸም ላይ እያሉ ተይዘዋል የተባሉት የህወሓት ልዩ ሃይሎች አና ሚኒሻዎች ሻምበል ጻዲቅ ኪሮስ፣ ብርሃኑ ፍጹም፣ ምከትል ሳጅን አሰፋ መአዛ፣ ዋና ሳጅን ሞገስ ደሳለኝ ፣ ሃይሌ አብርሃ እና ፈይሳ ተካ ናቸው።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎችን በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቅርቦ ለተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ጠይቋል።
ተጠርጣሪዎቹ ህገመንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለመናድ ሙከራ ወንጀል እና በሃገር ክህደት ወንጀል የተጠረጠሩ ሲሆን ከህወሓት እና ከኦነግ ሸኔ ጸረ ሰላም ቡድኖች ጋር በመቀናጀት ተልዕኮ በመፈጸም ላይ እያሉ በትግራይ መያዛቸውን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።
መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ የተከሳሸነት እና የምስክር ቃል መቀበሉን ጠቁሞ ለቀሪ ማለትም ከብሄራዊ መረጃ ደህንነት ተቋም የቴክኒክ ማስረጃ ለማስመጣት፣ ቀሪ የምስክር ቃል ለመቀበል፣ ያልተያዙ ግብረአበሮችን ለመያዝ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጿል።
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ከተጠርጣሪዎች ጋር በበቂ ሁኔታ ያልተገናኙና ያልተማከሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ተጨማሪ ጊዜ የሚፈቀድ ከሆነም አጭር ቀጠሮ ይሰጥ ሲሉም ተደምጠዋል።
ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድቤቱ ለመርማሪ ፖሊስ ከጀመረው ምርመራ አንጻር ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል ሲል ከጠየቀው 14 ቀናት ወስጥ 11 የምርመራ ቀናትን ፈቅዷል።
በታሪክ አዱኛ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.