Fana: At a Speed of Life!

ከመስቀል አደባባይ እስከ መዘጋጃ ቤት ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኙ 7 ህንፃዎች ታሪካዊ ይዞታቸው ተጠብቆ ይታደሳሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከመስቀል አደባባይ እስከ መዘጋጃ ቤት ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኙ 7 ህንፃዎች ታሪካዊ ይዞታቸውን እንደጠበቁ የሚታደሱ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመስቀል አደባባይ እስከ መዘጋጃ ቤት ድረስ እያከናወነ ባለው መልሶ መገንባትና የከተማ ማስዋብ ስራ ከግንባታው በተጨማሪ የተለያዩ የቦታ ዝግጅቶች እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ፕሮጀክቱ የሚያልፍባቸው መሥመሮች 7 የተለያዩ በቅርስነት የተመዘገቡና የሚታወሱ ህንጻዎች ያሉ ሲሆን፥ ህንጻዎቹም በመልሶ ማልማት ውስጥ የተካተቱ ታሪካዊ ይዞታቸውን እንደጠበቁ የሚታደሱና አገልግሎት ላይ የሚውሉ መሆናቸውም ተገልጿል።

ህንጻዎቹን ሲገለገሉበት የነበሩ ግለሰቦችና ተቋማትም ወደ ሌላ ቦታ የሚዛወሩ መሆኑንም የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክረታሪ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

ከዚህ ባለፈ ቅርሶቹ ሊፈርሱ ነው በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰትና የፈጠራ ወሬ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

ይህን በተመለከተ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ እያስተላለፉ የሚገኙ የብሮድካስትም ይሆን የኦንላይን ሚዲያዎች የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጠየቅ ትክለኛና ሚዛናዊ የሆነ መረጃ እንዲያስተላልፉም አሳስቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.