Fana: At a Speed of Life!

ከመንግስት ጥሪ ቢደረግልን ሰራዊቱን እንቀላቀላለን-በሚዛን አማን የሚኖሩ የቀድሞ ሰራዊት አባላት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህግ ማስከበር ዘመቻው የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ከመንግስት ጥሪ ቢደረግላቸው ሰራዊቱን እንደሚቀላቀሉ  በሚዛን አማን ከተማ  የሚኖሩ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ገለፁ።

የቀድሞ መከላከያ ሠራዊት አባላቱ የህግ ማስከበር ዘመቻውን መደገፍ ብቻ ሳይሆን በሃገር የማዳን ተልዕኮው ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል።

በሰልፉ ላይ የተገኙት የቀድሞ የሰራዊቱ አባላት መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉና  ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን  መሆናቸውን ገልጸዋል።

የቀድሞው ሰራዊት አባላቱ ከዚህ ሃገር የማዳን ዘመቻ ባሻገር ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታና የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት፣የውጪ ተፅኖና ሌሎችንም ጉዳዮች የተመለከቱ መፈክሮችን አሰምተዋል።

በአብዱ ሞሃመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.