Fana: At a Speed of Life!

ከማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አባላት 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ዓመታዊ መዋጮ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27 ቀን 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ከማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አባላት 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ዓመታዊ መዋጮ መሰብሰቡን አስታወቀ።
በዚህ ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተጠቃሚ ዜጎችን ቁጥር ወደ 40 ሚሊየን ከፍ ለማድረግ እንደሚሰራም ገልጿል።
የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የአባልነት እድሳትና ምዝገባ ዘመቻን አስመልክቶ ዛሬ በተሰጠ መግለጫ ላይ÷ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥር 32 ሚሊየን ደርሷል።
መጪውን የጥር ወር “የጤና መድህን ወር” ብሎ በመሰየም የአባልነት እድሳትና አዳዲስ አባላትን የመመዝገብ ተግባር እንደሚከናወንም ተናግረዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የጤና መድህን አስፈጻሚ አካላት የአባልነት ምዝገባ ዘመቻውን የመምራትና የማስተባበር ስራ እንደሚያከናውኑም ገልጸዋል።
መገናኛ ብዙሃንና ታዋቂ ግለሰቦችን በመጠቀም ስለ ዘመቻው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እንደሚከናውኑም ነው የጠቆሙት።
ከጤና መድህን አባላት 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ዓመታዊ መዋጮ መሰብሰቡን ገልጸው÷ ከዚህም ውስጥ አባላቱና ቤተሰቦቻቸው ላገኙት የሕክምና አገልግሎት ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ለጤና ተቋማት ክፍያ ተፈጽሟል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን በ2003 ዓ.ም በ13 ወረዳዎች በሙከራ ደረጃ የተጀመረና አሁን በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ተስፋፍቷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.