Fana: At a Speed of Life!

ከማስታወቂያ ጋር የተየያዘው የፌስቡክ ማሻሻያ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ፌስቡክ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን የሚያቀርቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለደንበኞች ተደራሽ የሚሆኑበትን መመዘኛ ማሻሻሉን አሳወቀ፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፌስቡክ ያደረገው ማሻሻያ የማስታወቂያዎችን ተደራሽነት ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

ድርጅቱ አሁን ላይ የደንበኞችን የኢ-ሜል አድራሻ እና ስልክ ቁጥርመረጃን የፌስቡክ ገጽንና የኢንስታግራም ገጽን ለማገናኘት በመጠቀም የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ተደራሽ እያደረገ ይገኛል፡፡

ይህ አካሄድ አንድ ሰው የተለያዩ ገጾችን ከፍቶ የሚጠቀም ቢሆንም የሚቆጠረው ግን እንደ አንድ ብቻ እንዲሆን አድርጎታል ሲል በያዝነው ሳምንት ባወጣው መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

ከዚህ በኋላ ፌስቡክ በኢሜልና በስልክ ቁጥር የሚገናኙ ገጾችን ደንበኛው ጥያቄ እስካላቀረበ ድረስ እንደማያገናኝ አሳውቋል፡፡

በሌላ አማራጭም ሰዎች ራሳቸው የሚለጥፏቸውን ማስታወቂያዎችና መረጃዎች ከኢንስታግራማቸው ወይም ከሌላ የፌስቡክ አካውንታቸው ጋር ማገናኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ይህ ማሻሻያ ሰዎች የሚያቀርቧቸው የማስታወቂያ ስራዎች ላይ የተሻለ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ያስችላል ሲል ድርጅቱ አሳውቋል፡፡

ይህ ግን በእለታዊም ሆነ በወርሃዊ የተመልካች ቁጥር ላይ የሚኖረው ተጽእኖ እንደሌለው ፌስቡክ አክሎ ማሳወቁን ቴክኤክስፕሎርን ጠቅሶ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት አስነብቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.