Fana: At a Speed of Life!

ከሞቱ ከ10 ሰዓታት በኋላ ዳግም ነብስ የዘሩት አዛውንት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከሞቱ ከ10 ሰዓታት በኋላ ዳግም ነብስ የዘሩት ዩክሬናዊት አዛውንት ብዙዎቹን እያነጋገሩ ነው።

ዩክሬናዊቷ የ83 ዓመት አዛውን ህይወታቸው ማለፉን በህክምና ባለሙያ እና በፖሊሶች ከተረጋገጠ ከአስር ሰዓታት በኋላ ዳግም ከሞት አምልጠው ነብስ ዘርተዋል ነው የተባለው።

አዛውንትዋ ባለፈው ሳምንት በቤታቸው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ የህክምና  ባለሙያዎች እና ፖሊስም መተንፈስ እንዳቆሙ እና እንደሞቱ ያረጋገጣሉ ቤተሰቦቻቸውም ለቀብር ሥነ ሥርዓቱ ዝግጅት ይጀምራሉ።

ነገር ግን ከዛ በኋላ የተፈጠረው ሁሉንም  ያስደነገጠ ነበር፤ ሞቱ የተባሉተት አዛውንት መሞታቸው ከተረጋገጠ ከ10 ሰዓት በኋላ በሕይወት የመኖር  ምልክቶች ያሳዩ ሲሆን፥ ከዚያ ወዲህም ሙሉ በሙሉ ማገገም ጀምረዋል።

ይህን ቀድማ ያወቀችው የአዛውንትዋ ሴት ልጅ እጇን በሰውነታቸው ላይ ስታደርግ ሙቀት እንደነበራቸው እንደተሰማትና በህይወት እንዳሉ እንደተረዳች ተናግራለች።

በፅኑ ታመሙ ተብለው ወደ ሆስፒታል የተወሰዱትን አዛውንት የተከታተሉት ዶክተርም መጀመሪያ እንደሞቱ ማረጋገጣቸውን ገልፀው በስራ ዘመናቸው እንደዚህ ዓይነት ክስተት አጋጥሟቸው እንደማያውቅ ተናግረዋል።

በመጨረሻም አዛውንቷ ምን እንደታያቸው ሲጠየቁ “መንግሥተ ሰማያት ነበር፤  አባቴን ጠራሁት! እዚያ መግኘት ለእሱ ቀላል እንደሆነ ለመጠየቅ ፈልጌ ነበር  እንደምንገናኝም አሰብኩ፤ ዓይኖቼን ከፍቼ ሳይ ግን ነርሶች ነጭ ልብስ ለብሰው ነበር! እነሱ መላእክቶች ናቸው ብዬ አሰብኩ ግን እነሱ በእርግጥ ሐኪሞች ነበሩ” ብለዋል።

በመጨረሻም እግዚአብሔር ምህረት አሳየኝ በማለት ተናግረዋል።

ምንጭ ፡-ኦዲቲ ሴንተራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.