Fana: At a Speed of Life!

ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ውጪ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው -የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልል መለያን የያዙ ሰሌዳዎችን የሚያስቀር ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሠራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎችን በተመለከተ ሚኒስቴሩ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም ፥ በቅርቡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ላይ አስፈላጊውን ግብዓቶች በማካተት እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መምራቱን አስታውሷል፡፡

ሆኖም ግን ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ውጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መመራቱን የሚገልጽ ዜና እየተዘገበ ስለመሆኑ አረጋግጠናል ብሏል ሚኒስቴሩ ፡፡

“በመጀመሪያ መረጃዉ የተሳሳተና ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ውጭ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን” ሲልም ገልጿል፡፡

በመቀጠልም ፥ “በቀድሞ አዋጁ የነበረዉ የተወሰኑ ክልሎችን ታርጋ ዝርዝር የያዘ አባሪ በዚህ ረቂቅ አዋጅ የቀረው መንግስት ተጨማሪ ክልሎች ሲወጡ በየጊዜዉ በአዋጁን ማሻሻል ሳያስፈልገዉ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችል ታስቦ መሆኑ ታውቆ የክልል መለያ ሰሌዳን ከተሸከርካሪዎች ላይ የማንሳት የረቂቅ አዋጁ ሀሳብና ይዘት አካል እንዳልሆን ሊታወቅ ይገባል” ሲልም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የመንገድ ትራንስፖርትን አስመልክቶ የፌዴራሉንና የክልል አስፈጻሚ አካላት የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር በማያሻማ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጎልበት ዘርፉ አስተማማኝ፣ የተቀናጀ፣ ዘመናዊና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ሆኖ እንዲራመድ የሚያስችል እንደሆነና በቅርቡም ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎና አስፈላጊዉ ማሻሻያ ተደርጎበት እንደሚጸድቅ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.