Fana: At a Speed of Life!

ከስደት ተመላሽ ሴቶችና ወጣቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ ዕድል ፈጠራ ኤጀንሲ እና ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ ሴቶችና ወጣቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አደረጉ።

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ ይፋ ያደረጉት ፕሮጀክት ከስደት ተመላሽ ሴቶችና ወጣቶችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት ነው።

የኢፌዴሪ ስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን እና የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ካምፓኒ የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳርይል ዊልሰን ፕሮጀክቱን ማስጀመሪያ ስምምነት ተፈራርመዋል ።

20 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት ፕሮጀክቱ 600 ከስደት ተመላሽ ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል ።

ፕሮጀክቱ በኦሮሚያ ፣ አማራ ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው የሚተገበረው።

በእነዚህ አካባቢዎች 150 ኪዮስኮችን የመገንባትና የመስሪያ ቦታ የማመቻቸት ዓላማ ያለው ሲሆን ተጠቃሚዎቹም ሱቆቹን ተቀብለው በቀጥታ ወደ ሥራ መግባት እንዲችሉ የግንባታ ሥራው በ6 ወራት ውስጥ ተጠናቅቆ ለእድሉ ተጠቃሚዎች እንደሚተላለፍ ተነግሯል።

ከስደት ተመላሽ ዜጎች ከሀገር ውጪ በነበሩበት ጊዜ  ገንዘባቸውን ወደ ሀገራቸው በመላክ በኢኮኖሚው ውስጥ የራሳቸውን አስተዋጽዖ ሲያበረክቱ የነበሩና የካበተ የሥራ ልምድ ያላቸው ስለሆኑ በመለስተኛ ድጋፍ ዘላቂ ሥራ ፈጥረው ለሌሎችም የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚችሉ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በአልዓዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.