Fana: At a Speed of Life!

ከቤተሰብ ገንዘብ ለማግኘት በሚል “የተቀናበረ የሰው እገታ” የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቤተሰብ ገንዘብ ለማግኘት በሚል “የተቀናበረ የሰው እገታ” የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የጎንደር ከተማ ሰላምና የህዝብ ደህንነት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ሰብለ ወልዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የተቀናበረ የሰው እገታ እንደተፈፀመ በማስመሰል የማታለል ወንጀል የፈፀሙት ሁለት ተጠርጣሪዎች በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሙሉጌታ መካሻ የተባለው ግለሰብ ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከባንክ ገንዘብ አውጥቶ የባጃጅ ትራንስፖርት ሲጠቀሞ የታገተ በማስመሰል፤ ቤተሰቦቹ አድራሻው ላይ አርማጭሆ ወረዳ ሮቢት አካባቢ ለሆነው አጋሩ ፍቃደ ደነቀው ለተባለው ተጠርጣሪ 400 ሺህ ብር እንዲከፍሉለት በስልክ ሲጠይቁ ሰንብተዋል።
የጎንደር ከተማ ደህንነትና ፖሊስ ከቤተሰቦች የደረሳቸውን መረጃ መሰረት በማድረግ የክትትል ስራ ማከናወናቸውን ባለሙያዋ ገልፀዋል።

በዚህም አጋቹ የጠየቀውን ገንዘብ ለመቀበል ሲሞክር እጅ ከፍንጅ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የገለጹት፡፡

ፖሊስ ምርመራ ሲያደርግም ታጋቹ የአጋቹ ተባባሪ ሁኖ በጋራ እንደፈፀሙት መረጃ በማግኘቱ “ታግቻለሁ” በማለት ቤተሰቦችንና መንግስትን ያታለለው ግለሰብ ለማምለጥ ቢሞክርም ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር መዋሉን ባለሙያዋ አክለዋል።
“ታጋች ነኝ” ያለው ተጠርጣሪ ለምን ይህን እንዳደረገ ሲጠየቅም ” ከቤተሰብ ገንዘብ ለመውሰድ” መሆኑን ተናግሯል።

እንዲህ አይነቱ ድርጊት በተለይ በተጠርጣሪ ወንጀለኞች ጉዳት ደርሶባቸው የፀጥታ አካላትን ድጋፍ የሚሹ እውነተኛ ተጎጅዎች አገልግሎት እንዳያገኙ አሉታዊ ጫና ስለሚኖረው ህብረተሰቡና ባለድርሻዎች መሰል ወንጀሎችን ለመከላከል ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በነብዩ ዮሐንስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.