Fana: At a Speed of Life!

ከቦርዱ ውጪ ይፋ የሚደረጉ የተመዝጋቢዎች ቁጥር ተቀባይነት እንደሌላቸው ቦርዱ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተቋሙ ውጪ የሚገለጹ ማንኛውም ዓይነት የመራጮች ምዝገባ ቁጥሮች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን አስታወቀ፡፡

የመራጮች መረጃን የሚያስተላልፉ አካላትም ከቦርዱ የሚያገኙትን ቁጥር ብቻ እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡

በዚህም መሰረት ቦርዱ በተለያዩ ጊዜያት የተመዘገቡ ጊዜያዊ መራጮችን ቁጥር እያሳወቀ እንደሚገኝ ነው የገለጸው፡፡

ምዝገባውን መረጃ በሚያጠናቅርበት ወቅት የምርጫ ክልል ማስተባበሪያ መዋቅሮቹን በመጠቀም መሆኑን ገልጿል፡፡

ከምርጫ ጣቢያ የሚገኙ መረጃዎችን በማጠናቀር ወደማዕከል የኦፕሬሽን ዴስክ የሚላከውም በምርጫ ክልል ማስተባበሪያ ቢሮዎች አማካኝነት መሆኑንም ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.