Fana: At a Speed of Life!

ከተማረክንም በህወሃት ጁንታ ሳይሆን በኢትዮጵውያን እና በኢትዮጵያዊነት ነው- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል እያካሄደ የነበረውን ህግን ማስከበር ዘመቻ አጠናቆ እና ህዝቡን በማረጋጋት ወደ ቀየው መመለስ መጀመሩን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ አስታወቁ።

የራያ ግንባር አዛዥ ሌተናል  ጄኔራል ባጫ ደበሌ ህግን በማስከበር እርምጃው በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሌተናል  ጄኔራል ባጫ ደበሌ በመግለጫቸው የመከላከያ ሰራዊቱ ሶስተኛ ምዕራፍ ህግን የማስከበር ዘመቻውን  አጠናቆ በደህንነት ስጋት ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ መመለስ ተሸጋግሯል ብለዋል።

ሰራዊቱ የፀጥታ ስጋት የሚታይባቸውን አካባቢዎችን በማረጋጋት ህብረተሰቡ ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ነው ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የጁንታው ቡድን በተለያዩ ከተሞች ሊፈፀማቸው የሚችሉ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶችን ለመከላከል ሰራዊቱ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

በትናትነው ዕለት የፅንፈኛው ቡድን አባላት  ሌተናል  ጄኔራል ባጫን  ማርከናል የሚል መረጃ ሲነዙ እንደነበር በመግለጫቸው ላይ ያነሱት ሌተናል ጄኔራሉ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እየፈረጠጠ ያለው ቡድን ምንም አይነት የመማረክ አቅም ብለዋል።

ከተማረክንም በህወሃት ጁንታ ሳይሆን በኢትዮጵውያን እና በኢትዮጵያዊነት ነው ሲሉ በመግለፅ የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር  በጋራ በመሆን መግለጫ እንደሚሰጡም ጠቁመዋል።

የጁንታው ቡድን አባላትን ለህግ ለማቅረብ የሚከናነው ስራዎች እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

በፋሲካው ታደሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.