Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ለትግራይ ክልል 100 ሚሊየን ብር እና 35 ሚሊየን ብር የሚገመት የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሚሊየን ብር እና 35 ሚሊየን ብር የሚገመት የቢሮ ቁሳቁስ፣ 3 አምቡላንስ እና 2 መኪናዎችን ለትግራይ ክልል ድጋፍ አደረገ ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መቐለ ከተማ በመገኘት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ለሆኑት ዶክተር ሙሉ ነጋ ድጋፉን አስረክበዋል ፡፡
በቆይታቸውም ከክልሉ አስተዳደር አመራሮችና ከመቐለ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚህ ወቅት ምክትል ከንቲባዋ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረግነው ድጋፍ ሲሆን አብሮነታችንን ፍቅራችንን እና ለህዝቡ ያለንን አክብሮት ለማሳየት ያደረግነው ነው ብለዋል።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች መሪዎች ከግል ፍላጎታችን ወጣ ብለን ስለህዝባችን ልንኖር ይገባል ያሉ ሲሆን በክልሉ የተረጋጋ ሰላም እስኪሰፍንና አገልግሎት አሰጣጡ ወደነበረበት እስኪመለስ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፉ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡሀ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች ፣የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች በህግ ማስከበሩ ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በዓይደር ሆስፒታል በመሄድ መጠየቃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.