Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ በአዲስ አበባ ባለቤታቸው የማይታወቁ ቦታዎች፣ ህንጻዎች እና ቤቶች መገኘታቸውን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ባለቤታቸው የማይታወቁ ቦታዎች፣ ህንጻዎች እና ቤቶች መገኘታቸውን አስታወቀ።
ከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ያሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከልና ወደ ህጋዊ መስመር ለማምጣት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ገልጿል።
ከነዚህ ተግባራትም ውስጥ አንደኛው እና ዋነኛው ህገ-ወጥ የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ ግንባታ ሲሆን ይህንኑ በከተማው የሚታየውን ህገ-ወጥ ድርጊት ለማጣራት እና መረጃ ለማሰባሰብ በየደረጃው ግብረሃይል በማደራጀት እና ህዝቡን በማሳተፍ ከአንድ ወር በላይ የማጣራት ስራ ሲሰራ መቆየቱን አንስቷል።
በዚህም ባደረገው ማጣራት ባለቤታቸው የማይታወቁ ቦታዎች፣ ህንጻዎች እና ቤቶች መገኘታቸውን አስታውቋል ።
ግብረ ሀይሉ ባደረገው ማጣራትም የደረሰባቸው ዋና ዋና ግኝቶቹን ገልጿል።
ከግኝቶቹ መካከልም በህገ-ወጥ መንገድ የታጠሩ እና ባለቤትነታቸውን ማረጋገጥ ያልተቻለ ቦታዎችን፣ በህገ-ወጥ መንገድ መገንባት የተጀመሩ ግንባታዎች መኖራቸውን እና ባለቤቶቻቸው ያልታወቁ ቤቶች እና ህንፃዎች መገኘታቸውን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ዛሬ ማምሻውን ባወጣው የጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል።
በማስታወቂያው መሰረትም በግኝቶቹ ላይ ውሳኔ ወስኖ እርምጃ ከመውሠዱ በፊት የኔ ነው የሚል እና ህጋዊ ማስረጃ አለኝ የሚል አካልም ሆነ ግለሰብ ከነገ ከጥቅምት 23 ን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት መረጃም ሆነ ማስረጃ በመያዝ ለዚሁ ጉዳይ በየክፍለ ከተማው በተዋቀረ ግብረሃይል ጋር በመቅረብ እንዲያስረዳ ማሳሰቡን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.