Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አቀፍ የመምህራን የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “መምህራን በቀውስ ውስጥ ይመራሉ ፣ መጪውንም ይተነብያሉ!” በሚል መሪ ቃል አምስተኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን ቀን የምስጋና እና የዕውቅና መርሐግብር ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀው የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩም በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ተካሂዷል።

በመርሃ-ግብሩም ላይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ወይዘሮ አዳነች በወቅቱም መምህራን እስከዛሬ ላደረጉት አስተዋፅኦ መመስገን እና ማበረታታት እንደሚገባ ገልጸው÷ የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን አስፈላጊውን ትኩረት ይሰጣል ብለዋል ።

አያይዘውም ትምህርት የእድገት ሁሉ መሠረት ነው፣ በእድገትም ሆነ በቴክኖሎጂ አደጉ የምንላቸው አገራት መሠረታቸው ትምህርት ነው ብለዋል ።

የምስጋና ፕሮግራሙ ዋና አላማም መምህራን እስከዛሬ ላደረጋችሁት አስተዋፅኦ መሆኑን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ÷ከፊታችን ባለው ግዜ በስነምግባር የታነጸ ፣ሀገሩን የሚወድ እና ለመለወጥ የሚጥር ትውልድ ለማፍራት መምህራን በትጋትና በፅናት መስራት አለባችሁ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል ።

በዚህ መርሀ ግብር ላይም በባለፈው የትምህርት ዘመን የላቀ አስተዋፆ ላበረከቱ 160 መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እውቅናና ሜዳሊያ መሠጠቱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጥህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.