Fana: At a Speed of Life!

‘ከተሞች ለሰላም‚ የተሰኘ የሠላም ምክክር ፎረም ነገ በአርባ ምንጭ ከተማ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)”ከተሞች ለሰላም” የተሰኘ አገር አቀፍ የሠላም ምክክር ፎረም ነገ በአርባ ምንጭ ከተማ ይካሄዳል፡፡

በሰላም ምክክር ፎረሙ ላይ ለመገኘት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ዛሬ ረፋድ ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡

ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ በተጨማሪ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የክልልና ከተማ አስተዳደር አመራሮችም በመድረኩ ይሳተፋሉ፡፡

በዛሬው እለትም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሚኒስተሮችና የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የአሬንጓዴ ልማት እና የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችንም ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱም በከተማ አስተዳደሩ እየተሰራ ከሚገኘው አሬንጓዴ ልማት የህዝብ መዝናኛ ፓርክ ባለፈ የአርባዎቹ ምንጮችንና የአዞ እርባታ ጣቢያውንም ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በነገው እለትም ፕሬዚዳንቷ ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከተማው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.