Fana: At a Speed of Life!

ከታላቁ ነብዩ መሐመድ ተምረን የአገራችንን ሰላምና አንድነት መጠበቅ አለብን – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነቢዩ መሐመድ የአንድነትና የሰላም ታላቅ መሪ በመሆናቸው ከእሳቸው ተምረን የአገራችንን ሰላምና አንድነት መጠበቅና ማጠናከር አለብን ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ ተናገሩ ።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ 1ሺህ 496ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በተከበረበት ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በግጭትና በግድያ ተግባር የተሰማራችሁ ‹‹ሽብር ፈጣሪነታችሁን፥ ግድያችሁንና አረመኔያዊነታችሁን አቁማችሁ፤ የአገራችንን ሰላም እንጠብቅ፥ አንድነታችንን እናክብር፥ አገራችንን እናልማ››ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ነብዩ መሐመድ የእምነት፣ እዝነትና የአንድነት፣ የሰላምና የእኩልነት ታላቅ መሪ መሆናቸውን የተናገሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ፥ ከነብያችን ተምረን የአገራችንን ሰላምና አንድነት እንድንጠብቅና እንድናጠናክር አደራ እላለሁ ብለዋል።
እርስ በርሳችን እንመካከር፣ እንተባበር፣ እንቀራረብ፤ እንዋደድ፥ አንድ እንሁን ሲሉም መክረዋል።
በአገራችን ውስጥ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት አይዟችሁ ልንላቸውና ፥ ከጎናቸው እንድንቆምም ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ አሳስበዋል።
በአሰፋ አሕመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.