Fana: At a Speed of Life!

ከቴክኖሎጂ ጋር ወደፊት የሚራመድ ብቁ ዜጋን ማፍራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቴክኖሎጂ ጋር ወደፊት የሚራመድ ብቁ ዜጋን ማፍራት እንደሚገባ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ገለጸ።

የ2013 ዓ.ም  የቴክኖሎጂ፣ ክህሎትና ጥናትና ምርምር ክልላዊ የውድድር አውደ ርዕይ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በሲዳማ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው  በዚህ የውድድር አውደ ርዕይ ላይ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ቀርበዋል።

በዚሁ ወቅት  የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ÷ከዚህ በፊት ዘርፉን አንቀው የያዙትን ችግሮች ለማስወገድ መንግስት በትኩረት እየሠራበት ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ከዘመኑ ጋር ለመዘመን ለውጥ የሚያመጡ ባለሙያዎችን ማበረታታት እና እውቅና መስጠት እንደሚያስፈልግም ነዉ የተናገሩት፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የትምህር ቢሮ ሀዋለፊ አቶ በየነ በራሶ በበኩላቸው÷አዋጭና ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማፍለቅ አዕምሮ እንዲበለጽግ መስራት ይቀድማል ብለዋል፡፡

በመሆኑም በክልሉ በትምህርት ዘርፍ ችግር ፈቺ ትዉልድን ለማፍራት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በተለይ ፈጠራን በማበረታታት የአካባቢዉን ህብረተሰብ ችግሮች የሚፈቱትን በመስራት ትልልቅ ዉጤቶች አንዳስገኙም ገልጸዋል፡፡

በዚህ በመጀመሪያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ የተዘጋጀዉ የፈጠራ አዉደ ርዕይና ዉድድር በ 16 የሙያ ዘርፎች ፈጠራቸዉን የሚያቀርቡ የፈጠራ ስራዎችን አሳታፊ አድርጓልም ነው ያሉት፡፡

አካል ጉዳተኞችም  ጭምር የአዕምሮ ፈጠራ ስራዎቻቸዉን በዚህ ዉድድር ማቅረባቸዉንና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እየታየበት መሆኑን ደግሞ የክልሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህር ስልጠናና ሳይንስና ቢሮ ሀላፊ አቶ አሻግሬ ጀምበሬ ገልጸዋል፡፡

ዉድድሩ እስከ መጋቢት 23  ቀን 2013 የሚቆይ መሆኑንም  ነው የተገለጸው።

በሀይማኖት ወንዲራድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.