Fana: At a Speed of Life!

ከቻይና ውጭ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ በላይ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከቻይና ውጭ ባሉ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ በላይ መድረሱ ተገልጿል።

በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ወቅት 93 በሚደርሱ የዓለም ሀገራት ውስጥ መስፋፋቱ ነው የተነገረው።

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ 3 ሺህ 735 የሚሆኑ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ 101 ሺህ 927 የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

በዚህ መሰረት ከቻይና ውጭ 21 ሺህ 114 ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸው ተመላክቷል።

በአፍሪካ ቫይረሱ በግብጽ፣ አልጀሪያ፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ካሜሮን፣ ቱኒዚያ፣ ቶጎ እና ናይጀሪያ መከሰቱ ተነግሯል።

ምንጭ፦ ሺንዋ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.