Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊና ማህበራዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ከንቲባዋ ጉዳዩን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የዘንድሮ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ እሴቱን ጠብቆ ባማረና በደመቀ ሁኔታ በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል ብለዋል።
 
የከተማችን ህዝብ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ላሳየው አስተዋይነት የተሞላው በሳል እንቅስቃሴ አድናቆቴንና አክብሮቴን መግለጽ እፈልጋለሁ ነው ያሉት።
 
“እኛም በጎንደር ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል፤ ስለተደረገልን ደማቅ አቀባበል የክልሉን፣ የከተማውን አመራሮችና ነዋሪዎችን ከልብ አመስግናለሁ” ብለዋል ።
 
ለአዲስ አበባም ይሁን ለመላው ኢትዮጵያ ድምቀትና ሃብት የሆነው የጥምቀት በዓል፣ ምዕመኑ በነቂስ ወጥቶ ተሳትፎበት በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትንም አመስግነዋል፡፡
 
በዚህም የእምነት አባቶች፣ የፀጥታ ሃይሎች፣ የከተማዋ ወጣቶች፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.